የአቅም ግንባታ ድጋፎች
በ2022 የህግ አውጭ ወቅት፣ የኦሪገን የህፃናት እንክብካቤ እና የቅድመ ትምህርት የሰው ኃይልን ለማረጋጋት እና ለማስፋፋት እና መሠረተ ልማታችንን ለወደፊት የፌዴራል ኢንቨስትመንቶች ለማዘጋጀት ወደ $100 ሚሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ ለስልታዊ ኢንቨስትመንቶች እንዲውል አሳልፈናል። ይህ ትቅል የህፃናት እንክብካቤ የአቅም ግንባታ የድጋፍ ፈንድን (Child Care Capacity Building Grant Fund) የሚያካትት ሲሆን፣ ይህም ተጨማሪ ልጆችን ለማገልገል የሚችሉ አዲስ ተቋማትን ለመጀመር ወይም ነባር ተቋማትን ለማስፋፋት ከአዳዲስ እና ነባር የህፃናት እንክብካቤ አቅራቢዎች ጋር በቀጥታ ለሚሰሩ ማህበረሰብ አቀፍ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣል።
እንዴት ማመልከት እችላለሁ?
Seeding Justice በኦሪገን ውስጥ ባሉ አምስት በብዛት የሚነገሩ ቋንቋዎች የሚሰራ ለተጠቃሚ ምቹ የሆነ የመስመር ላይ መተግበሪያን በማዘጋጀት ሂደት ላይ ነው። ማመልከቻዎች በአስተባባሪ ኮሚቴ እና በ Seeding Justice ሰራተኞች የሚገመገሙ ሲሆን፣ አስተባባሪ ኮሚቴው አንድን ማመልከቻን ካፀደቀ ወይም ውድቅ ካደረገ በኋላ፣ አመልካቾች በ Seeding Justice ሰራተኞች ማሳወቂያ ይደርሳቸዋል።
ተጨማሪ ድጋፍ
የህፃናት እንክብካቤ አቅም ግንባታ የድጋፍ ፈንድ አስተባባሪ ኮሚቴ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ለመተግበር ወይም ለማስፋፋት በሚሰሩበት ጊዜ የጋራ የመማር እድሎች እና ድጋፎችን ለማሸነፍ የጋራ የመማር እድሎች እንዲኖራቸው ለማድረግ እና ቀጣይነት ያለው የጋራ ትምህርት እና የቴክኒክ ድጋፍ ድጋፍ ለመስጠት አቅዷል። Seeding Justice ከድጋፍ ተቀባዮች ጋር የድጋፍ ስምምነቶችን ለመፈረም እና የፀደቁ ድጋፎችን ለማሰራጨት የሚሰራ ሲሆን፣ የገንዘብ ድጋፉ የሚፈቅድ ከሆነ አመልካቾች ለተጨማሪ ዙር እርዳታ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።
ብቁ የሚሆነው ማነው?
የልጅ እንክብካቤ መርጃ እና ሪፈራሎች
የቅድመ ትምህርት ማዕከላት
የጋራ የሠራተኛ አስተዳደር ትረስቶች
501(ሐ)(3) ደረጃ ያላቸው ወይም በ501(ሐ)(3) ድርጅቶች በበጀት የተደገፉ የባህል ልዩ ማህበረሰብ አቀፍ ድርጅቶች።
የጎሳ መንግስታት፣ የትምህርት ተቋማት እና የአገልግሎት ወረዳዎችን ጨምሮ ሌሎች ማህበረሰብ ተኮር ድርጅቶች
የገንዘብ ድጋፉንን እንዴት መጠቀም ይቻላል?
የመጀመሪያ የሥራ ማስኬጃ ወጪዎች
የልጆች እንክብካቤ የስራ እቅድ ማዘጋጀት
የመመዝገቢያ አቅም ላይ ለመድረስ እና የስራ ማስኬጃ ወጪዎችን ለማስቀጠል ከ3-6 ወራት ወጭዎችን ለመሸፈን
የልጆች እንክብካቤ ፈቃድ ወይም ሌሎች መስፈርቶችን ለማሟላት እና/ወይም ተጨማሪ ልጆችን ለማገልገል ያስችል ዘንድ ቦታውን ለማደስ
ለአስገዳጅ ስልጠናዎች የባለሙያ ትምህርት ድጋፍ ወይም ለኮንትራቶች ለነፃ ተጨማሪ የሥልጠና ፕሮግራሞች
ስራ መጀመርን ወይም መስፋፋትን የሚደግፉ አቅርቦቶች እና ቁሳቁሶች
ድጋፍፕቹ የተለያዩ ወጪዎችን ለመሸፈን ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ፣ ለምሳሌ:
የልጆች እንክብካቤ ስራ ስልጠና
እድሳት እና ካፒታል ፕሮጀክቶች
ጥቅም ላይ የሚውል ቦታን ለማስፋፋት
ግብይት እና የግብይት ቁሳቁሶችን ለማዳበር
የሰው ኃይል ድጋፍ
የቦታዎችን ማሻሻያ ወይም መስፋፋትን ለመደገፍ እቅድ እና የቴክኒክ እርዳታ
ጉርሻዎችን፣ የሰው ኃይል ድጋፍ፣ ከቅጥር አስተዳዳሪዎች ጋር መስራት፣ ወዘተ ጨምሮ የሰራተኛ ቅጥር እና ሰራተኛን የማቆየት ጥረቶች ለማገዝ
እነዚህ ድጋፎች የሚተዳደሩት በ Seeding Justice ሲሆን፣ ይህም ድርጅት እነዚህን አይነት ድጋፎች የማስተዳደር እና ከማህበረሰብ አጋሮች ጋር በመስራት ልምድ ያለው የአካባቢ እና ታማኝ የማህበረሰብ አቀፍ ድርጅት ነው። እነዚህ ድርጅቶች የዚህ ድጋፍ አስተዳዳሪ ሆነው የተመረቱበት ምክንያትም ጉዳት ከደረሰባቸው ማህበረሰቦች እና ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው እና የገንዘብ ድጋፍን ለ " ችግረኛ " ማህበረሰቦች ከላይ ወደ ታች የሚያዳርስ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆነ የባህል አቀራረብ የሚከተሉ በመሆኑ ነው። እነዚህ ድጋፎች በህብረተሰቡ ውስጥ እና በአቅራቢዎች እጅ ፍትሃዊ እና ወቅታዊ በሆነ መንገድ መድረሳቸውን ለማረጋገጥ ጠንካራ የዘር፣ የፆታ እና የኢኮኖሚ ፍትህ ማጣሪያዎችን ይጠቀማሉ።
ውሳኔዎች እንዴት እየተደረጉ ነው?
እንደ በጀት ወኪልነቱ፣ Seeding Justice የገንዘብ አያያዝን እና የእርዳታ አሰጣጥ ሂደቱን የሚከታተል ከማህበረሰብ ተኮር የህፃናት እንክብካቤ ባለድርሻ አካላት የተውጣጣ አስተባባሪ ኮሚቴ ለማዘጋጀት ይረዳል። አስተባባሪ ኮሚቴው ተገቢውን ተደራሽነት፣ የስጦታ አሰሳ፣ ቀጣይነት ያለው የቴክኒክ ድጋፍ እና ለድጋፍ ተቀባዮች እገዛ፣ ወዘተ ለማረጋገጥ ለሚያስፈልጉ የሰው ሃይል ምንጮችን ይመድባል። ከዚህም ሌላ፣ ስለ ፈንድ እንቅስቃሴዎች፣ የአጠቃቀም/የስራ ደረጃ እና ሊያጋጥሙ ስለሚችሉ መሰናክሎች በተመለከተ መደበኛ ሪፖርቶችን ለህግ አውጪው ያቀርባሉ።
በአስተባባሪ ኮሚቴው ውስጥ የሚሳተፉ ድርጅቶች የሚከተሉትን የሚያካትቱት ሲሆን፣ ነገር ግን በእነዚህ ብቻ አይገደቡም፥